የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ከስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ETRSS-2 ለተሰኘችው ሁለተኛው የመሬት ምልከታ ሳተላይት ፕሮጀክት የማማከር አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ በዘርፉ በኮሪያ ሀገር የሰለጠኑ ባለሙያዎችን እና በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባለሙያዎችን በጋራ በማሳተፍ እቅዳችንን እንደሚያሳካልን እንተማመናለን ብለዋል።
ፕረዘዳንቱ በዩንቨርስቲው ያሉትን የዘርፉ ባለሙያዎች እና በውጪ ሀገራት የሚገኙትን በማቀናጀት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩ E ETRSS-2 የተሰኘችዉ ሁለተኛው የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለማምጠቅ የሚስችል ሀገራዊ ፕሮጀክት በመቅረጽ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡