የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የፌደራል ጤና ሚኒስተር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በተገኙበትና ፕሮግራሙን በከፈቱት በሚሊኒየም አዳራሽ ሲካሄድ በቆየው የአገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን ጉብኝት ላይ የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያቤት ሰራተኞች፣ ዩኒቨርሲቲዎች ፣የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ የሀገራችን ህዝቦች ኤግዚቢሽኑን ጎብኝተዋል፡:
ይህ ኤግዚቢሽን በሀገራችን ያሉ የህክምና ግብአት ምርትና ኤኖቬሽን ላይ የተሰማሩ የምርምር ማእከላት እና ዩኒቨርሲቲዎች የፋርማሲዉቲካል ዉጤቶቻቸዉን እንዲያቀርቡ ለማስቻል ነዉ፡፡